አንድን ነገር ደግሞ ደጋግሞ በመስራት የተለየ ውጤት መጠበው እብደት ነው።

From the Editor

የሀገራችንን ፖለቲካ በቅርብ ለምንከታተል ሁሉ አዲስ ባይሆንም ህወሀት/ኢህአዴግ ዴሞክራሲአዊ አለመሆኑን እየተናነቀውም ቢሆን “ውስጣዊ ዴሞክርሲ መገንባት ተስኖን ነበር” ሲል አምኗል።

ዝርዝሩን ከ Ethiopian Reporter ሊንክ መመልከት ይችላሉ። ታዲያ መነሳት ያለበት ጥያቄ

በውስጡ ዴሞክራሲያዊነት የሌለው  የፖለቲካ ድርጅትና መንግስት ከዚህም በላይ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እንዳመኑትም  ውስጡ “የበሰበሰ፣ የነቀዘና ኪራይ ሰብሳቢነትና በአድርባይነት የተዋሀደው” ፓርቲና መንግስት እንዴት ነው የዴሞክርሲ ስርአትን ለመመስረት ፣ፍትህን ለመመገንባት፣  ለሀገር ጥቅም የሚበጅ ስርአትን ለማምጣት ብቃት የሚኖረው?፧ የራሱ ቤተሰብ የሚበላው የሌለው ሰው ለሌላ ሰው እርዳታ እሰጣለሁ ቢል የሚመስል ነገር ይሆናል?

ስለሆነም ስርአቱ ስህተቱን እንዳማነው ሁሉ፣ ጊዜ ወስዶ ራሱን ለማስተካከል የሚሰራውን ይስራ ።የታመመ ሰው ህመሙን ማስታመም አግባብ ነው፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ኢህአዴግ “በጥልቅ እስኪታደስ” (ያውም ከሆነለት) ቁጭ ብሎ ይጠብቅ ማለት ወይም ዴሞክራሲያዊ ስርአትን የሚሻ ህዝብ ዼሞክራሲያዊ  አይደለሁም ብሎ ባመነ ፓርቲና መንግስት መመራት አለበት ማለት በፍጹም ስለሀገር አለማሰብ ፣ ፍፑም ህሊና ቢስነት ወይም ተራ ስግብግብነት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የተሻለ መሪ ሊኖረው የሚገባው ታላቅ ህዝብ ነው።

ሁኔታወን ለማሻሳል ደግሞ በሽተኛው ራሱ አይደለም ሀኪም መሆን ያለበት። ስለዚህ ህወሀት/ኢህአዴግ መፍትሄ ፍለጋውን ለኢትዮጵያ ህዝብ መተው ይኖርበታል። ሀኪሙ የሚገኘው ከህዝቡ ውስጥ ነው። ሀኪሙ ህዝቡ ነው። በርግጥ በመፍትሄ ፍለጋው ውስጥ የበሽተኛው ድምጽም መሰማት ይኖርበታል። የያንዳንዱ በሽታ የሀገር በሽታ ነው እና ወደፊት ለመጓዝ ማንንም ቢሆን ወደ ሓላ ጥሎ መሆን የለበትም ። ለዚህ ነው ደግመን ደጋግመን ለሀገር የሚሆን ዘላቂ መፍትሄ ከተፈለገ ሁሉም ባለድርሻ የሚሳተፍበት ብሄራዊ መግባባት   ባስቸኳይ መጀመር አለበት የምለው። ይህ ሳይሆን ህወሀት/ኢህአዴግ ከነበሽታው ሀኪምም እኔ ብቻ ነኝ ብሎ አሁን በሚሄድበት ጎዳና ከቀጠለ ፤ ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ እንደሚባለው አንድ ቦታ ላይ መዳከር እንጂ መሻሻል ሊመጣ ከቶ አይችልም። ይሀንንማ ህወሀት/ኢህአዴግ አ25 አመት  ሞክሮ ውጤት ሊያሰገን አልቻለም። እንደሚባለውም አንድን ነገር ደግሞ ደጋግሞ በመስራት የተለየ ውጤት ለማግኘት መሞከር እብደት ነው። ኢትዮጵያ አዲስ አካሄድ አዲስ ጅምር ያሰፈልጋታል።