በመተከል ስለተካሄደው የዘር ተኮር ጭፍጨፋ

መስከረም 8፣ 2013 September 19, 2020

ለተከበሩት ዶክተር አብይ አህመድ

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር

አዲስ አባባ ኢትዮጵያ

ጉዳዩ፦ መተከል ስለተካሄደው የዘር ተኮር ጭፍጨፋ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆይ

በስሜን ምእራብ ኢትዮጰያ በመተከል አካባቢ ቡለን፣ ማዳራ ወንበራ  በተባሉት አካባቢወች ከጳጉሜ ወር መጀመሪያ ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም በአማራና በአገው ማህበረ ስቦች አባላት በሆኑት ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሆነ  መረጃዎች ያሳያሉ።

በአካባቢው ባሉ መንደሮች ውስጥ ታጣቂዎች ህዝቡን በየትምርት ቤቱ ስብስበው ካስገቡ በኋላ የአማራና የአገው ማህበርስብ ተወላጆችን ለይተው አሰቃቂ በሆነ መልክ መጨፍጨፈፋቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች የሚደርሱ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህም መረጃ የክቡርነትዎ ጽ/ቤት እንዳገኘውም ሙሉ ዕምነታችን ነው።

ይህን ሁኔታ ማድበሰበስም ሆነ ማጋነን አደጋውን በትክክል ከማየት የሚጋርድ ሲሆን፣ መፍትሄውንም ከእውነታው ጋር የማይጣጣም ሊያደርገው ይችላል።

ሰለዚህም፤

1)        ከነዚህ የማድበሰበስም ሆነ የማጋነን ተግባሮች መንግስትም ሆነ የፖለቲካ ደርጅቶች ሊቆጠቡና እውነተኛውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ሊያደርጉ ይገባል

2)       ይህን በተወሰነ ማህበረሰብ አባል በሆኑ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ፍጅት በስሙ መጥራትና ህብረተስቡ እንዲረጋጋ አጣዳፊና አጥጋቢ እርምጃ መውስድ ያሰፈልጋል

3)       ይህን ወንጀል ሲፈጽም የአካባቢው የጸጥታ ሀይል እንዴት ሊያውቅ እንዳልቻለና መከላክልስ እንዲት እንዳልቻለ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ ያስፈልጋል

4)       ይህን ወንጀል የፈጸሙና ያስፍጸሙ ሀይሎች ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ እና የህግ የበላይነትን ያለአንዳች ማወላወል እነዲሰፍን ማድረግ ያስፈልጋል

5)       አካባቢያዊም ሆነ አለም አቀፍ ህብረተስቡም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እያደገ ከመጣው ጽንፈኛነትና ማነነትን ላይ ያነጣጠር ጥቃት አጽንኦት ሰጥቶ እንዲከታተለውና ይህ ጉዳይ በኢትዮጰያ ውስጥም ሆነ በአካባቢው ተጨማሪ ጥፋት ከማድረሱ በፊት እንዲቆም አስፈላጊውን ትኩረትና ተጽእኖ እንዲያደርጉ አበክረን እናሳስባለን

ግልባጭ

  • ለከቡር ጠቅላይ ሚኒሰቴር ጀስተን ትሩዶ፣ ኦታዋ, ካናዳ
  • ለተባበሩት መንግስታት የዘር ማጥፋት መከላከያ ዲፓርትመንት
  • ለሚመለከታቸው አለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ተከላካይ ድርጅቶች
  • ለዶክተር ዳንኤል በቀለ ፣ የኢትዮጰያ ስብአዊ መብት ድርጅት፣

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *